ባለፉት ሁለት ዓመታት የታዮትን ለውጦች የዳሰሰና በ20 ምሁራን የተዘጋጀ ወጥ መጽሐፍ ለገበያ...

ባለፉት ሁለት ዓመታት የታዮትን ለውጦች የዳሰሰና በ20 ምሁራን የተዘጋጀ ወጥ መጽሐፍ ለገበያ ቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የለውጡ ቡድን (የአሁኑ ብልፅግና ፓርቲ) ኢትዮጵያ  ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተካሄዱ ለውጦችን የዳሰሰ መጽሐፍ ለገበያ ቀረበ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በኢትዮጵያ የተከናወነውን የፖለቲካ ለውጥ ሂደትና ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚያመላክተውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ “Ethiopia in the Wake of Political Reforms” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ዛሬ በይፋ ተመርቋል።
በለውጡ ማግስት በሀገሪቱ ውስጥ የታዮ ጉዳዮችን ተንተርሶ የተዘጋጀው አራት ክፍሎችና 616 ገፆችን መያዙ ታውቋል።
በ20 ኢትዮጵያዊ ምሁራን የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ በሀገሪቷ ባለፉት ሁለት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ጉዳዮች የተካሄደውን ለውጥ የዳሰሰ መሆኑ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተነግሯል።
ኅብረተሰቡ ስለ ለውጡ ያለውን ግንዛቤና የለውጡን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ያመላከተ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የመጽሐፉ ምረቃ ላይ የተገኙ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጋዜጠኞች መጽሐፉን በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል።

LEAVE A REPLY