በአቶ ልደቱ ላይ ሕገ መንግስቱን በመናድ የሚል ከሰ ቀረበ

በአቶ ልደቱ ላይ ሕገ መንግስቱን በመናድ የሚል ከሰ ቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አቶ ልደቱ ሕገወጥ መሳሪያ በመያዝ በሚለው ክስ በዋስ መለቀቃቸውን አስታውሶ፤

ግለሰቡ አሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያሉት ሕገ መንግሥቱን በመናድ በሚለው ተጨማሪ ክስ መሆኑን ይፋ አደረገ።
ለፍርድ ቤት አቶ ልደቱን በቀደመው ጉዳይ በዋስ መልቀቁን በጽሑፍ ያቀረበው የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ፤ “ግለሰቡ በምስራቅ ሸዋ ዞን የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ በሚል አዲስ ክስ ስለተመሰረተባቸው መልሰን በፖሊስ መዝገብ ቁጥር 171/2013 አስረናቸዋል” ሲል በደብዳቤው ላይ አስታውቋል።
ይህ ደብዳቤ ለተከሳሽ ጠበቆችም በግልባጭ እንዲደርስ የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መርምሮ ብይን ለመስጠት ለ26/2/2013 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል።
የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ አቶ ልደቱ አያሌውን በአንድ መዝገብ ፈትቶ፣ በሌላ ማሰሩን የሚያሳይ ማስረጃ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የሰጠው ትናንት ረቡዕ ነበር።
በምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ትዕዛዝ የተሰጠላቸው አቶ ልደቱ አያሌው ትናንት  የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተገኙት በ9/2/2013 ዓ. ም ችሎት በቀረቡበት ወቅት የተሰጡት ሁለት ትዕዛዞችን ለመከታተል መሆኑን ገልጸው፣ አሁን ተከፈተ የተባለውን አዲስ ነገር ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY