አል ዐይን ኒውስ በ 5 ቋንቋዎች በአዲስ መልክ ሥራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

አል ዐይን ኒውስ በ 5 ቋንቋዎች በአዲስ መልክ ሥራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከአራት ዓመት በፊት ሥራ የጀመረው አል ዐይን ኒውስ ከአማርኛ ቋንቋን በተጨማሪ በሌሎች 4 ዓለም ዐቀፍ ቋንቋዎች ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

አል ዐይን የዜና ተቋም አዲስ የዲጂታል ሚዲያውን ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 14 በሁሉም ቋንቋዎች ይፋ አድርጓል።
ተቋሙ እንደገለጸው ከሆነ በዘርፉ ፈር ቀዳጅ ለመሆን ባለው ቁርጠኝነት ላይ በመመርኮዝ፣ ሙያዊ እና ተዓማኒ ይዘቶችን እጅግ በጣም ዘመናዊ በሆኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ይዞ መቅረብ ጀምሯል።
 ለዕይታዎ በሚማርክ መልኩ በአዲስ አቀራረብ ፣ በአዲስ የድኅረ ገጽ ዲዛይን (al-ain.com) ፣ በተጨማሪም በስማርት ስልኮች እና በተለያዩ የዲጂታል ሚዲያ መተግበሪያዎች ላይ የሚነበቡ፣ የሚደመጡና የሚታዩ ዘገባዎችን በአምስት ቋንቋዎች ( በአረብኛ ፣ በፈረንሳይኛ ፣ በፋርስኛ ፣ በቱርክኛ እና በአማርኛ) ይዞ እንደሚቀርብም
አስታውቋል።
 “አይንዎ በዓለም ላይ ነው” የሚል መርህ አንግቦ መረጃዎችን በፍጥነት ለማድረስ እንደሚሠራ የገለጸው ተቋሙ፤ በርከት ያሉ ጥበብ የተሞላባቸው ቪዲዮዎችን ፣ እውነትን ፈትሸው የሚያቀርቡ ዘጋቢ ፊልሞችን ጨምሮ ለተለያዩ ጉዳዮች ሽፋን በመስጠት እንደሚሠራም አስታውቋል።

LEAVE A REPLY