የኢትዮጵያ ዮንቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች በሁለት ወር ትምህርት ሊመረቁ ነው

የኢትዮጵያ ዮንቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች በሁለት ወር ትምህርት ሊመረቁ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት አቋርጠው የነበሩ ዩኒቨርስቲዎች በጥቅምት ወር መጨረሻ ሳምንት አንስቶ ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ናቸው ተባለ።

የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 እስከ 30/2013 ዓ. ም የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ አይዘነጋም።
የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ደቻሳ ጉርሙ ከጥቅምት ወር አንስቶ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ተማሪዎቹ ቀርተዋቸው የነበሩ ኮርሶችን በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ እንዲያጠናቅቁ መወሰኑን ፣ እንዲሁም ከዚያ በኋላ ደግሞ የኮሮናቫይረስ ሁኔታን በማየት ለተቀሩት ተማሪዎች ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኮቪድ-19ን እየተከላከሉ ትምህርትና ሥልጠናን ለማስቀጠል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 እሰከ 30/2013 ዓ. ም አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ተነግሮ ነበር።
በቅርቡ ዩኒቨርስቲዎች በሀዋሳ ከተማ ለሦስት ቀናት ባካሄዱት ስብሰባ ትምህርት ለማስጀመር መወሰናቸውን የጠቆሙት ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ፤ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ብቻ ነው መማር የሚችሉት ሲሉም አሳስበዋል።
በሀገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ላለፉት ሠባት ወራት ትምህርት ለማቋረጥ  ተገደዋል።
ትምህርት ለመጀመር ከተዘጋጁት ዩኒቨርስቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የወለጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐሰን የሱፍ ከጥቅምት 23 እስከ 30 2013 ዓ. ም ባሉት ቀናት ውስጥ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን እንቀበላለን ሲሉ ለቢቢሲ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።
በቀጣይ  የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ያሉትን ተማሪዎች ጥሪ እናደርጋለን ያሉት የዮንቨርስቲው ፕሬዝዳንት፤ ከሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች የአንደኛ መንፈቀ ዓመት ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ለሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ዝግጅት ላይ በነበሩበት ወቅት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ቤተሰባቸው ለመመለስ መገደዳቸውንም አስታውሰዋል።

LEAVE A REPLY