የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ መደበኛ ትምህርት ህዳር 7 ስለሚጀምር ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲልኩ ጥሪ...

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ መደበኛ ትምህርት ህዳር 7 ስለሚጀምር ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲልኩ ጥሪ አቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ምስራቅ ሸዋ ዞን ትምህርት ጽሕፈት ቤት፤ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው መደበኛ ትምህርት ህዳር 7 እንደሚጀመር አስታወቀ።

መደበኛ ትምህርት በሁሉም ት/ቤቶች ህዳር 7 ለማስጀመር ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ ነው ያሉት የዞኑ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ታዬ ዶሪ፤ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደትን ጥቅምት 16 ለመጀመር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ መምህራን ለረጅም ወራት ሳያስተምሩ በመቆየታቸው ምክንያት አስፈላጊ ሥልጠና መምህራን ተሰጥቶ፣ ወደ መማር ማስተማር መገባት እንዳለበት ስለታመነ ከታሰበው ጊዜ ሊዘገይ ችሏል ብለዋል።
በዞኑ 1ሺኅ 520 ተጨማሪ የማስተማሪያ ክፍሎች መሠራታቸውንና በተለያዩ ድጋፎች የተገኙ 43 ሺኅ መጽሐፎችም ወደ ለትምህርት ቤቶች መከፋፈላቸውን የጠቆሙት አመራሩ፤ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ለሁሉም ተማሪዎች በነፍስ ወከፍ ሁለት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስኮች እንዲደርሳቸው እንደተደረገና በየትምህርት ቤቱ የእጅ መታጠቢያዎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
መንግሥት ትምህርትን በተስተካከለ ማስኬድ የሚያስችል በቂ የሆነ የቁሳቁስ አቅርቦት በማቅረብ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ በመሆኑ፤  ወላጆች ልጆቻቸውን ያለ ስጋት ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ መልእክት አስተላልፈዋል።

LEAVE A REPLY