በጎርፍ መጥለቅለቅ ሥራ ያቆመው አዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

በጎርፍ መጥለቅለቅ ሥራ ያቆመው አዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዋሽ ወንዝ ሙሌትን ተከትሎ በጎርፍ በመጥለቅለቁ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው የአዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ለ49 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውና 32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ይህ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ፣ በውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ከነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ይታወሳል።
በወቅቱ ከተርባይን ወለል እስከ ተርባይን ሮተር ማገናኛ ዘንግ ድረስ ያሉት የኤሌክትሮ-መካኒካል እቃዎች በውሃ ተውጠው ነበር ፡፡ በዚህ ምክንያት ለሁለት ወራት አገልግሎት አቋርጦ የነበረው ጣቢያ አንድ ዩኒት ወደሥራ ማስገባት በመቻሉ ጣቢያው በከፊል ሥራ እንዲጀምር አስችሎታል።
ቀሪውን አንድ ዩኒት ሥራ ለማስጀመር በሂደት ላይ እንደሚገኝ የገለፀው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ይህም በቅርቡ እውን እንዲሆን ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

LEAVE A REPLY