ኮኬይን በቦሌ ኤርፖርት በኩል ልታስወጣ የሞከረች አንዲት ታይላንዳዊ በቁጥጥር ሥር ዋለች

ኮኬይን በቦሌ ኤርፖርት በኩል ልታስወጣ የሞከረች አንዲት ታይላንዳዊ በቁጥጥር ሥር ዋለች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አደገኛ እፅ ስታዘዋውር የተገኘች ታይላንዳዊት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ዋለች።

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የኢንተለጀንስ አደገኛ ዕፅና ሬዲዮ መገናኛ ዳይሬክቶሬት ስር የሚገኘው ፣ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ምክትትል ዳይሬክቶሬት ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ትናንት ከምሽቱ አራት ሰዐት በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ባደረገው ክትትል ነው ተጠርጣሪዋን ሊይዝ የቻለው።
ተጠርጣሪዋ ከአዲስ አበባ ወደ ታይላንድ ባንኮክ ጉዞ ማድረግ ላይ ነበረች። የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዋ አደንዛዥ ዕፁን በልብስ ውጫዊ የሻንጣ አካል በመደበቅ ለማሳለፍ ሙከራ ብታደርግም ሁለቱ የፀጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪዋና በእጇ ላይ የነበረው 2 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የቡድኑ መሪ ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY