በአፋር ክልል የተገደሉት የሁለቱ የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች አስከሬን አዲስ አበባ ገባ

በአፋር ክልል የተገደሉት የሁለቱ የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች አስከሬን አዲስ አበባ ገባ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአፋር ክልል በሥራ ላይ እያሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን ያጡት ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች አስከሬን አዲስ አበባ ገባ።

የሁለቱ ሟቾች አስከሬን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በአፋር የሽኝት ሥነ ሥርዓትም ተደርጎለታል።
አቶ ሙላት ፀጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ የሚባሉ የተባሉት ሁለት ሠራተኞች የተገደሉት ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር በማኅበራዊ  ሚዲያ ትስስር ገጹ ላይ ገልጿል።
የሠራተኞቹ አስከሬን ከአፋር ክልል ዛሬ፣ ጥቅምት 18 2013 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባም ገብቷል። ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያን  ጨምሮ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ሠራተኞችም ለሠራተኞቹ አስከሬን ወደየአካባቢያቸው (ቀዬአቸው) ሽኝት ማድረጋቸው ታውቋል።
ሁለቱ ሠራተኞች በተተኮሰ ጥይት በተገደሉበት ወቅት የመቁሰል አደጋ ያጋጠመው ሌላኛው የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኛ አቶ ደምሴ ታምሬ፤ የሕክምና ክትትል እያደረገ መሆኑንም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

LEAVE A REPLY