ምርጫው በግንቦት ወይም በሰኔ ወር እንደሚካሄድ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ አስታወቁ

ምርጫው በግንቦት ወይም በሰኔ ወር እንደሚካሄድ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በነፃነት ታጋይዋ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቄሳ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ የፊታችን ግንቦት ወይም ሰኔ ወር ላይ ለማካሄድ ማቀዱን ይፋ አደረገ።

ባለፈው ዓመት በወርሀ ነሐሴ ሊካሄድ የነበረው ሥድሥተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከተራዘመ በኋላ፤ በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ የተሰየመው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠር በመቻሉ ምርጫውን ማካሄድ ይቻላል የሚል ውሳኔ ቢያሳልፍም ቁርጥ ያለው የምርጫ ጊዜ ሳይታወቅ ቆይቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ከኮቪድ 19 ወረረሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ ማካሄድ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚዲያ አካላትና የሲቪክ ማኅበራትን በማሳተፍ ዛሬ ምክክር አድርጓል።
 ቦርዱ ለውይይት ባቀረበው መነሻ ሀሳብም 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በግንቦት ወር የመጨረሻ ሁለት ሳምንታት፣ አልያም የሰኔ ወር የመጀመርያ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ለማካሄድ እቅድ እንዳለው ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ገልጸዋል።
ምርጫ ቦርድ በቅድመ እቅድ ደረጃ ፕሮግራሙን  ያሳውቅ እንጂ፣ የጊዜ ሰሌዳውን በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን እንደሚያካትትም እወቁልኝ ብሏል።

LEAVE A REPLY