በአሶሳ ግጭት አስነስተዋል የተባሉ 32 ግለሰቦች ከ7 እስከ 21 ዓመት በሚደርስ እስራት...

በአሶሳ ግጭት አስነስተዋል የተባሉ 32 ግለሰቦች ከ7 እስከ 21 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአሶሳ ግጭት በማስነሳት ተጠርጥረው የተከሰሱ 32 ግለሰቦች ላይ ከሠባት እስከ ሀያ አንድ ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ውሳኔ መተላለፉ ተሰማ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የአሶሳ እና አካባቢዋ አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት ሰኔ 2010 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ ግጭት በማስነሳት በተከሰሱ 32 ግለሰቦች ላይ ነው ቅጣቱን ያስተላለፈው።
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እንደገለጸው ከሆነ ሰኔ 16፣ 17 እና 18 ቀን 2010 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የ17 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ ከፍተኛ የሆነ የንብረት ውድመትም ደርሷል፡፡
ይህን ተከትሎ ከጉዳዩ ጋር ንክኪ አላቸው በሚል የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ በ32 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሶሳ እና አካባቢዋ አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት፣ ቀደም ሲልም በእነዚሁ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝት ውሳኔ አሳልፏል።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በአሶሳ ከተማ በዋለው ችሎት ደግሞ በእነዚህ 32 ተከሳሾች ላይ ከሠባት ዓመት እስከ 21 ዓመት የሚደርስ የጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉ ተረጋግጧል።
ዛሬ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተላለፈባቸው 32 ሰዎች መካከል 15ቱ በሌሉበት ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆን፤ በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ የፍርድ ሂደቱን ከጨረሱ በኋላ ከየትኛውም ሕዝባዊ መብት ለሥስት ተከታታይ ዓመታት ታግደው እንዲቆዮ ውሳኔ አሳልፏል።

LEAVE A REPLY