ትናንት ምሽት አማራዎች በምዕራብ ወለጋ ዘግናኝ ጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፀመባቸው

ትናንት ምሽት አማራዎች በምዕራብ ወለጋ ዘግናኝ ጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፀመባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ትናንት ምሽት በምዕራብ ወለጋ ነዋሪ የሆኑ ንጹሃን ዜጎች ላይ ዘር ተኮር የሆነ ዘግናኝ የሆነ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተረጋገጠ።

የጠቅላይ ማኒስትር ዐቢይ መንግሥትም ይሁን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ብሔር ተኮር ጥቃቱ መፈጸሙን ቢያምንም ጥቃቲን ያደረሰው ኦነግ ሸኔ ነው የሚል የተለመደ አስተያየት ከመስጠቱ ውጪ፣ የአደጋውን መጠንና የሟቾቹን ቁጥር አልገለፀም።
አሁን ላይ የአካባባውን ኗሪዎችና የተጎጅ ቤተሰቦችን ዋቢ ያደረጉ አንዳንድ ምንጮች እንደሚገልጹት ከሆነ ትናንት በስብሰባ ሰበብ በተወረወረባቸው ቦንብ ሕይወታቸውን ያጡና ለአካል ጉዳት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ50 ይበልጣል።
እንደ አካባቢው ምንጮች ጥቆማ ከሆነ የቦንብ ውርወራዎቹን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ነፍሳቸውን ለማዳን በሚሸሹበት ወቅት በጥይትና በገጀራ ጥቃት የተፈጸመባቸውም ሰዎች ቁጥር በርካታ ነው ተብሏል።
በዚህ ጥቃት ላይ የክልሉ የጸጥታና የሚሊሻ አካላት እንዲሁም የዞንና የወረዳ አመራሮች መኖራቸውን የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ የኦነግ ሸኔ አባላቱ ስብሰባ አለ በሚል በአካባቢው የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን በየመንደሩ እየተዘዋወሩ ሲጠሩና ምሽት ላይ በአንድ ቦታ እንዲከማቹ ሲያደርጉ ነበር? በማለትም ይጠይቃሉ።
ባለፉት ሁለትና ሦስት ወራት ብቻ በተለያዮ የሀገሪቱ ክልሎች በተለይም በኦሮሚያ አንዳንድ ዞኖች በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጥቃት ለማስቆም የሚያስችል እርምጃ ሥልጣን ላይ ያለው የፌደራል መንግሥቱ አለመውሰዱ ትናንት ምሽት የሥድሥት ወር ሕጻንን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እንዲፈጸም በር ከፍቷል።

LEAVE A REPLY