መንግሥት ለዜጎች አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ ብፁዕ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ

መንግሥት ለዜጎች አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ ብፁዕ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግሥት ለዜጎች አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ እና ወንጀለኞችንም ለፍርድ እንዲያቀርብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አሳሰበች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ፣ በደቡብ ክልል ቤንች ሼኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያና ሰብኣዊ ጥሰት በይፋ አውግዘዋል።
የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባ፤ በዓመታዊ ስብሰባ ላይ እያለ ይህንን አሳዛኝ ጥቃት የሰማው መሆኑን ያስታወሱት አቡነ ማትያስ፤ ድርጊቱ ሲኖዶሱንና ቤተ ክርስቲያኗን በእጅጉ ያሳዘነ ኢ ሰብአዊ ጥቃት መሆኑንም ይፋ አድርገዋል።
ቤተ ክርስቲያኗ በግፍ ለተገደሉና ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ልባዊ ሐዘኗን ትገልጻለች ያሉት ፓትሪያርኩ፤
መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት፣ በፍቅርና በአንድነት በመተሳሰብ በፍቅር እንዲኖሩ፣ ለጋራ ሰላምና አንድነት እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY