አምንስቲ መከላከያ ሠራዊቱ ለምን እና በማን ትእዛዝ እንደወጣ መጣራት አለበት ሲል አሳሰበ

አምንስቲ መከላከያ ሠራዊቱ ለምን እና በማን ትእዛዝ እንደወጣ መጣራት አለበት ሲል አሳሰበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ ከ54 የማያንሱ ብሔራቸው አማራ የሆኑ ሰዎች ተገድለዋል ሲል በመግለጫው ላይ ይፋ አድርጓል።

አምነስቲ የሀገር መከላከያ አካባቢውን ጥሎ መውጣቱን ተከትሎ የኦሮሞ ነጻነት ጦር አባላት ሳይሆኑ እንደማይቀሩ የተጠረጠሩ ታጣቂዎች ጥቃቱን መፈጸማቸውን ገልጿል።
መከላከያ ሠራዊት አካባቢውን ለምንና አንዴት ጥሎ መውጣት እንዳስፈለገው መጣራት ይገባዋል ያለው አምንስቲ፤ በጥቃቱ ሴቶች እና ሕጻናት ጭምር መገደላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በተያያዘ ዜና የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሞሳ ፋኪ ማሕማት፤ የአማራ ብሔረሰብ ተወላጅ በሆኑ ንጹሀን ዜጎች መገደላቸውን አጥብቀው እንደሚያወግዙ አስታወቁ።
 መንግሥት ጥቃቱን የፈጸሙ ቡድኖችን ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበት ያሳሰበው የድርጅቱ መግለጫ፤ በማኅበረሰቡ መካከል የሚከሰት ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን በመጥቀስ፤ ሁሉም አካል ግጭትን ከሚያባብስ ትርክት እንዲቆጠብም ተማፅኗል።

LEAVE A REPLY