ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ትናንት ምሽት በምዕራብ ወለጋ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር እስካሁን ድረስ በተሰበሰበ መረጃ 32 መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።
በጠንካራ የሰብኣዊ መብት ተሟጋቹ ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን በየጊዜው የሚደርሱ ግድያዎችና የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን በፍጥነት በማጋለጥ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ይገኛል።
በቀጣይ ተጠናክረው የሚቀርቡ መረጃዎችን በፍጥነት ወዲያው ማድረሱን እንደሚገልጽ የጠቆመው የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን አሁን ባለው ሁኔታ የሟቾችና የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ከወዲሁ ፍንጭ ሰጥቷል።
በስፍራው 60 የሚሆኑ የተለያዮ መሣሪያዎችን የታጠቁ ታጣቂዎች በሦስት ቀበሌዎች ውስጥ እየተዘዋወሩ ይህንን ዘግናኝ ጥቃት መፈጸማቸውን ያስታወቀው የኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን በጥቃቱ ሕጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎች ተጎድተዋል ብሏል።
እሰካሁን ድረስ የአሮሚያ ክልል መንግሥትም ሆነ የፌደራል መንግሥቱ ጥቃቱን ከማመን ውጪ የደረሰውን የጉዳት መጠን በዝርዝርና በአይነት አልገለጹም።