በአዲስ አበባ ኢንተርኔት ሊቋረጥ፣ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች ሊታሠሩ ይችላሉ ተባለ

በአዲስ አበባ ኢንተርኔት ሊቋረጥ፣ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች ሊታሠሩ ይችላሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ህወሓት የጦርነት ትንኮሳ መጀመሩን ተከትሎ ትናንት ሌሊት በፌደራል መንግሥትና በህወሓት መካከል የተጀመረው ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ በአዲስ አበባ የኢንተርኔት አገልግሎት ሊቋረጥ እንደሚችል ተነገረ።

በሁለቱ ኃይሎች መካከል ያለውን ውጥረት ተንተርሶ በተለይም የመከላከያ ሠራዊት ህልውናን የሚፈታተኑ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ እንዲሁም ከህወሓት ግንኙነት አላቸው ተብለው በሚጠረጠሩ ግለሰቦች ላይም የእስር እርምጃ እንደሚወሰድ ተገምቷል።
የተለያዮ ታማኝ ምንጮች እንደገለፁት ከሆነ በአዲስ አበባ ኢንተርኔትና ስልክ አለመቋረጡን ተከትሎ ከላይ የተጠቀሱት አካላት የመከላክያን ህልውና የሚፈታተኑና ሕዝብን ግራ የሚያጋቡ፣ ብሔር ተኮር ግጭቶችን የሚቀሰቅሱ ጽሑፎች በጥፋት ቡድኖች በኩል በማኅበራዊ ቡድኖች በኩል እየተሠራጩ ናቸው።
በመሆኑም መንግሥት አሁን ካለበት አፋጣኝ ሀገራዊ ጉዳይ አኳያ እንዲህ አይነቱ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የመከላከያ ሠራዊቱን  ስም የማጠልሸቱ ሥራ ተጠናክሮ ከቀጠለ በአዲስ አበባ የኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጥ በአክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞችና የተለያዮ ግለሰቦች ላይ የእስር እርምጃ ሊወስድ ይችላል ነው የተባለው።

LEAVE A REPLY