ኢዜማ ሕወሓት የኢፌዴሪ መከላለከያ ሠራዊት ላይ የከፈተውን ጥቃት በፅኑ ያወግዛል

ኢዜማ ሕወሓት የኢፌዴሪ መከላለከያ ሠራዊት ላይ የከፈተውን ጥቃት በፅኑ ያወግዛል

የ ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሕወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የኢፌዴሪ መከላለከያ ሠራዊት ላይ የከፈተውን ጥቃት በፅኑ ያወግዛል። በተለያየ ጊዜ ሕወሃት ሲያስተላልፋቸው የነበሩ የሥርዓት አልበኝነት ጥሪዎች እና በክልሉ ሕግን ተላልፎ ሲፈጽም የነበራቸው ድርጊቶች አልበቃ ብለው የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ምልክት የሆነው መከላከያ ሠራዊታችን ላይ የፈፀመው ጥቃት በፍፁም በዝምታ የሚታለፍ እንዳልሆነ እናምናለን። የነበረው ችግር በንግግር መፈታት ከሚችልበት ምዕራፍ አልፎ አሁን የደረሰበት ደረጃ መድረሱ በጣም አሳዝኖናል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሀገር አንድነት እና ሰላምን ለማስከበር የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በመደገፍ የኢዜማ አባላት እና አመራር ከጎኑ እንደምንሰለፍ እናሳውቃለን። በሚወሰዱ እርምጃዎች ሰላማዊ ዜጎችን ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስባቸው አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ እንደሚገባው ለማስታወስ እንወዳለን።

የትግራይ ሕዝብ የሚወሰደው እርምጃ ለሀገር አንድነት እና ሰላም ማስከበር ብቻ እንደሆነ በመረዳት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲቆም እንጠይቃለን። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ይህንኑ በመረዳት አብሮነታችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ እና ለሰላም እና ደህንነት እንቅፋት የሚሆኑ ማንኛውንም እንቅስቃሴዎች ከማድረግ ተቆጥበን አካባቢያችንን በንቃት እየጠበቅን ለሰላም እና ደህንነት መከበር ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ትብብር እንድናደርግ የአደራ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

LEAVE A REPLY