ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሶማሌ ክልል ሕዝብና መንግሥት በህወሓት ላይ በሚወሰደው እርምጃ ከፌዴራል መንግስት ጎን እንደሚቆሙ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ አረጋገጡ።
ህወሓት ኋላ ቀር፣ ከፋፋይ እና ዘረኛ ሥርዓት በሀገሪቱ ላይ ዘርግቶ ቆይቷል ያሉት ሙስጠፌ፤ በዚህም በሶማሌ ክልል ሕዝብ እና በሀገር ሽማግሌዎች ላይ በተለያዩ ወቅቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፀም ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
ህወሓት ከለውጡ በኋላ በሶማሌ ክልል በተለያዩ ብሄሮች እና የሃይማኖት ተከታዮች መካከል ግጭት በመፍጠር አካባቢው እንዳይረጋጋ ቢሠራም፤ በሕዝቡና በክልሉ መንግሥት ጥረት መክሸፉን ያስታወሱት የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት፤ ዛሬም ቢሆንም ትንኮሳው የቀጠለ በመሆኑ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ይህን በመከላከል ለሀገር አንድነት እንዲሠሩ መልእክት አስተላልፈዋል።