የአሜሪካና እንግሊዝ ህወሓትና ፌደራል መንግሥቱ ሊደራደሩ ይገባል አሉ

የአሜሪካና እንግሊዝ ህወሓትና ፌደራል መንግሥቱ ሊደራደሩ ይገባል አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የትግራይና የፌደራል መንግሥት የገቡበትን ውጥረት ሊያረግቡ እንደሚገባ የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግሥታት አሳሰቡ።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ ሁለቱም ወገኖች የገቡበትን ውጥረት እንዲያረግቡ ከመጠየቁ ባሻገር  ለሰላማዊ ሰዎች ደህንነት ቅድሚያ ሊሰጡ እንደሚገባም አሳስቧል።
የእንግሊዝ መንግሥትም በተመሳሳይ መልኩ አዲስ አበባ ላይ ባለው ኤምባሲው አማካይነት በትግራይ ክልል ያለው ውጥረት በአፋጣኝ እንዲረግብ በዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ስም ጠይቆ፣ የሰላማዊ ዜጎቻቸውን ደህንነት ሁለቱም ወገኖች እንዲያስጠብቁም ምክር ለግሷል።

LEAVE A REPLY