ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ሲያካሂድ ትናንት የሚኒስትሮች ምክር በትግራይ ክልል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፀደቀ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ባደረገው አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ መንግሥት በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93/1/ሀ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን አስታውቋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት መግለጫ አክሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈጻሚ እንደሚሆን ማስታወቁ አይዘነጋም።
አዋጁን የሚያስፈፅም ፣ በኢፌዲሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተወጣጡ አባላት ያሉት ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ተደርጓል።
‘‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ሀይል’’ የሚል መጠሪያ የተሰጠው አዋጅ መደንገግ ያስፈለገበትን ምክንያት የሀገርን ሰላምና ሕልውና፣ የሕዝብንና የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ እና ሀገሪቷን ወደ ሁከትና ብጥብጥ የሚወስዱ ማናቸውንም ድርጊቶችን የመከላከል ሕገ መንግሥታዊ ሓላፊነትን መሠረት ባደረገ መልኩ መሆኑ ተነግሯል።