በትግራይ ክልል ከምሽት 2 ሰዐት እስከ ጠዋት 12 ሰዐት አስቸኳይ አዋጁ ተግባራዊ...

በትግራይ ክልል ከምሽት 2 ሰዐት እስከ ጠዋት 12 ሰዐት አስቸኳይ አዋጁ ተግባራዊ እንዲሆን ታዘዘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በትግራይ ክልል የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መተግበር እንደጀመረ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።

አዋጁን የሚያስፈፅሙ ግብረ ኃይል አባላት፣ እንዲሁም እውቅና ከሚሰጣቸው ሰዎች እና ተሽከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ሰው ወይም ተሽከርካሪ መመሪያውን ተግባራዊ እንዲያደርግም ታዟል።
አዋጁ ተፈፃሚ በሚሆንበት የትኛውም የትግራይ ክልል ቦታ ከምሽት 2 ሰዐት እስከ ንጋት 12 ሰዐት መንቀሳቀስ አይቻልም ተብሏል።
ከግብረ ኃይሉ ፍቃድ ውጭ ማንኛውም ሰልፍ ፣ በአደባባይ ወይም በቤት ውስጥ ስብሰባ ማድረ፣ እንዲሁም 4 እና ከዛ በላይ ሆኖ በቡድን መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ያለው አዋጁ፤ ከመከላከያ ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ሌሎች ፍቃድ ከተሰጣቸው የፀጥታ አካላት ውጪ ማኛውም የጦር መሳሪያም ሆነ ጉዳት የሚያደርሱ የተለያዩ እቃዎችን ይዞ መንቀሳቀስ አጥብቆ የተከለከለ እንደሆነም አስታውቋል።

LEAVE A REPLY