ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በፌደራል መንግሥትና በህወሓት መሀል የተጀመረውን የለየለት ጦርነት ተከትሎ የመቀሌ፣ ሽሬ፣ አክሱም እና ሁመራ ኤርፖርቶች ለበረራ አገልግሎት ዝግ እንዲሆኑ መደረጋቸው ታወቀ።
የኢትዮጵያ ሲቨል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዐት ጀምሮ የመቀሌ፣ ሽሬ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ ናቸው ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ በተመሳሳይ ሁሉም የሚመለከታቸው አካሎች ወይም ኤርሜንስ በተገቢው የመገናኛ ዘዴ በ(ኖታም) እንዲያውቁት መደረጉን ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይፋ አድርጓል።
እስካሁን ድረስ በመንግሥት በኩል ይፋዊ የሆነ ማረጋገጫ ባይሰጥበትም በትግራይ መቀለ የሚገኘው የአየር መቃወሚያ ትናንት ምሽት በፌደራል መንግሥት አየር ኃይል ጀቶች እንደተደበደበና ከአገልግልት ውጪ እንዲሆን መደረጉ እየተነገረ ነው።