ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል ልዮ ኃይል በጋራ በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ ዳንሻ ከተማን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራቸውና ከህወሓት ቁጥጥር ውጪ ማድረጋቸው ታወቀ።
በሁለቱ ጥምር ኃይል ጥቃት የደረሰበትና ከፍተኛ ኪሳራ ያጋጠመው የህወሓት ልዮ ኃይልና ሚሊሺያ ጦር በድንጋጤ አካባቢውን ለቅቆ መሸሹን ተከትሎ ዳንሻ በአሁን ሰዐት በአማራ ክልል ልዮ ኃይልና በአካባቢው ሚሊሺያ ሥር ትገኛለች።
የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ልዮ ኃይል በተገኘው ድል በመነቃቃት ወደ ሁመራ የገሰገሰ ሲሆን በዛ አካባቢ የሚገኘውን የህወሓት ጦርም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይደመስሳል ተብሎ ተገምቷል።