ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 30 ይጀመራል የተባለው የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ይፋ አደረገ።
ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጪ በተቀሩት ክፍሎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ 19 የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ እቅድ ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በከተማዋ ለመጀመር የታቀደው የገጽ ለገጽ ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል ነው የተባለው።
ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም መሰጠት የጀመረው የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል የገጽ ለገጽ የክለሳ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ግን ቢሮው አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ በማያጋልጥ ሁኔታ ጥቅምት 30/2013 ትምህርት ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ ስለመሆናቸውም ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ መግለጫ መረዳት ተችሏል።