ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጭቃኔ የተሞላበት ግድያና ጥቃት ያደረሱ 24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸው ተነገረ።
ዘግናኝ የግድያ ጥቃትና የንብረት መውደም ባደረሱ የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላት ላይ የክልሉ ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ መውሰዱን ያስታወቀው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፤ በተለይም በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጭቃኔ የተሞላበት በኦነግ ሸኔና የክህደት ኃይል በሆነው ህወሓት አቀናባሪነትና ደጋፊነት በንፁሃን ላይ የተወሰደው እርምጃ በጣም አሳዛኝ ነበር ብሏል።
ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ የኦሮሚያ ፖሊስ ባደረገው ክትትል በተለያዩ አቅጣጫዎች በምዕራብ ኦሮሚያ እና በደቡብ ኦሮሚያ በአጠቃለይ በኦነግ ሸኔ ላይ በተደረገ ክትትልና በተወሰደው እርምጃ፤ እስካሁን 24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሲደመሰሱ፣ 26 የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ አባላት ደግሞ እንደተማረኩና 23 የሚሆኑት በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለጸጥታ ሀይል መስጠታቸው ተገልጿል።