በትግራይ በተከታይ የአየር ድብደባዎች ይካሄዳሉ መባሉን ተከትሎ ነዋሪዎች ስጋት ላይ ናቸው ተባለ

በትግራይ በተከታይ የአየር ድብደባዎች ይካሄዳሉ መባሉን ተከትሎ ነዋሪዎች ስጋት ላይ ናቸው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አሕመድ ዓሊ መቀሌና በሌሎች በተመረጡ የትግራይ ክልል ከተሞች በሚገኙ የህወሓት የጦር ካምፖች ላይ ያተኮረ የአየር ድብደባ እንደሚካሄድ መግለጻቸውን ተከትሎ የትግራይ ነዋሪ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነው ተባለ።

የብልፅግና ፓርቲ መሪ ትናንት ምሽት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው በትግርኛ ለትግራይ ሕዝብ ባስተላለፉት መልእክት የአየር ጥቃቱ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ እንዳልሆነ ጠቁመው፤ የአውሮፕላን ድብደባው፤ ለሀገርና ለሕዝብ አደገኛ ነው ብለው የጠሩት ኃይል የያዛቸውን ቦታዎች ብቻ ዒላማ ያደረገ እንደሆነም አረጋግጠዋል።
በዚህ ሂደት ውስጥ ያልታሰበ አደጋ እንዳይመጣ ነዋሪዎች በከተማ አካባቢ ተሰብስበው የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲቀንሱ አጥብቀው ማስተላለፋቸውን ተከትሎ የትግራይ ሕዝብ በከፍተኛ ፍራቻ ውስጥ እንደሚገኝ የተለያዮ ዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ጭምር እየዘገቡ ናቸው።
ህወሓት አራት ኪሎ ቤተ መንግሥትን በተቆጣጠረበት ወቅት ወደ ትግራይ ያሸሻቸው በርካታ ከባድ የጦር መሣሪያዎች ተደብቀው ተቀምጠውበታል ተብለው የሚጠሩ አካባቢዎች እና ከሰሜን እዝ በተዘረፉ ከባድ ሮኬቶች በተከማቹበት ቦታዎች ላይ የሚካሄደውን ድብደባ ተከትሎ የጥፋት ቡድኑም ሌላ ችግር ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
በክፋትና ተንኮል የበለፀገው ህወሓት በትጥቅ ትግል ዘመኑ ወቅት በሀውዜን ነዋሪ ላይ የፈጸመውን የጭካኔ ተግባር አሁንም በምስኪኑ የትግራይ ሕዝብ ላይ ከአየር ድብደባው ጋር በተያያዘ ይደግመው ይሆናል ተብሎ ተገምቷል።

LEAVE A REPLY