በአዲስ አበባ በተለያዮ ሥፍራዎች ለመከላከያ ሠራዊት አባላት የሚሆን ደም ልገሳ ተካሄደ

በአዲስ አበባ በተለያዮ ሥፍራዎች ለመከላከያ ሠራዊት አባላት የሚሆን ደም ልገሳ ተካሄደ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዮ ሥፍራዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ሀገራዊ ግዳጅ ላይ ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት አባል የሚውል የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሂደዋል።

በተመሳሳይ የጉሌሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ ሠራተኞች እና ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ አካሂደዋል።
 ጽንፈኛው ህወሓት የፈጸመውን አስነዋሪ ተግባር ተከተሎ ግዳጅ ላይ ለሚገኘው፣ ከሀገር አልፎ ለቀጠናዊ ሰላም ሚናው የጎላ ለሆነው መከላከያ ሠራዊት  ሕዝቡ ከጎኑ መሆኑን ለማሳየት የታቀደበት የደም ልገሳ መርሀግብር ነገና በተከታታይ ቀኖች ውስጥ  በሁሉም ሥፍራዎች ይቀጥላል ተብሎ ተገምቷል።

LEAVE A REPLY