የህወሓት አመራሮች ሊሸሹበት ይችላሉ ተብለው የሚጠሩ የድንበር አካባቢዎች በከፍተኛ ጥበቃ ውስጥ ሆኑ

የህወሓት አመራሮች ሊሸሹበት ይችላሉ ተብለው የሚጠሩ የድንበር አካባቢዎች በከፍተኛ ጥበቃ ውስጥ ሆኑ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሱዳን በጋዳሪፍ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በህወሓት ውስጥ በሚገኝ የሽብር ቡዳን ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ተከትሎ ሱዳን በጋዳሪፍ በኩል ያለውን ድንበር መዝጋት መጀመሯን ከወዲሁ ይፋ አደረገች።
በምስራቅ ጋዳሪፍ ግዛት ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነው ድንበር ከዛሬ ጀምሮ ዝግ መደረጉን ያስታወቁት የሱዳን የአካባቢው ባለሥልጣኖች፤ ቀጣይ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስም ድንበሩ ዝግ ሆኑ እንደሚቆይም አረጋግጠዋል።
ቀደም ብሎ ሱዳን በከሰላ ግዛት በኩልም ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ደንበር መዝጋቷ አይዘነጋም። የከሰላ ግዛት አስተዳዳሪ ፈታህ አል ራሀማን አል አሚን፥ ካሳለፍነው ሀሙስ ጀምሮ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ከምትዋሰንባቸው ድንበሮች አንዱ በሆነው ከሰላ ግዛት አካባቢ ያለው የድንበር ዝግ መሆኑን ገልጸዋል።
ሰሞኑን የፌደራል መንግሥት በህወሓት ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ የተለያዮ ጎረቤት ሀገራት የመዘዋወሪያ ድንበሮቻቸውን መዝጋታቸው፣ ጥቃቱ እያስበረገገው ያለውን የህወሓት ቡድን አባላት መጠጊያና መሸሺያ እንደሚያሳጣ በመነገር ላይ ነው።
መንግሥትም በተመሳሳይ በህወሓት ውስጥ ሆነው ላለፉት ሁለት አመታት ለውጡን ለማደናቀፍ ከመጣር ባሻገር አሁን ወደለየለት የሽብርተኝነት ተግባር የገቡት አካላት ከትግራይ በመሸሽ ከሀገር ለመውጣት ጥረት ያደርጉባቸዋል የተባሉ የድንበር አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ ጦር በማሠማራት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ልዮ ጥበቃና ክትትል እያደረገ ይገኛል ተብሏል።

LEAVE A REPLY