የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት ሕግ አስፈጻሚን ተክተው እንዲሠሩ...

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት ሕግ አስፈጻሚን ተክተው እንዲሠሩ አዘዘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል ጣልቃ በመግባት ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ዛሬ መወሰኑን አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋምና ሌሎች ውሳኔዎችን መወሰኑን ይፋ አድርጓል።
የትግራይ ክልል በክልሉ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በማድረስና በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁ ጉዳት በማድረሱ ህገ መንግሥቱን ማስከበር አስፈላጊ ሆኗል ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉዳዮን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ በዚህም መሠረት የፌዴራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 359/95 መሠረት ውሳኔው ተፈጻሚ እንደሚሆንም አስታውቋል።
“የትግራይ ክልል መንግሥት ሕገ መንግሥታዊና የፌዴራል ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት በመፈፀም የፌዴሬሽኑን ሕልውና አደጋ ላይ የጣለ ስለሆነ ይህንን ድርጊት ማስቆም ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል” ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፤ በዚህም መንገድ የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ መግባት አስፈላጊ መሆኑን ከመጠቆም ባሻገር፣ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ጋር በተጣጣመ መልኩ የፌደራል ፖሊስን ወይም የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ፣ ወይንም ሁለቱንም በክልሉ እንዲያሠማራ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
የትግራይ ክልል ምክር ቤት እና የክልሉ ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል እንዲታገድ፣ ለፌደራል መንግሥቱ ተጠሪ የሆነና ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የወሰነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚኖረውንም ሥልጣን በዝርዝር  አስቀምጧል።
በዚህ መሠረት ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሓላፊዎች ይመድባል፣ ህግና ሥርዓት መስፈኑን ያረጋግጣል፣ አግባብ ባለው ህግ መሠረት በክልሉ ምርጫ የሚከናወንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ የክልሉን እቅድና በጀት ያፀድቃል፣ በፌደራል መንግሥት የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል።

LEAVE A REPLY