ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግሥት በትግራይ የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ዓላማው ስግብግቡን የመቀሌ ጁንታ ለሕግ ተገዥ የማድረግና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን ማስጠበቅ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለፁ።
በማኅበራዊ ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት እርምጃው ከማንም በላይ ሠፊውን ትግራዋይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “መንግሥት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ወንድምና እህት ትግራዋይን ማንነታቸውን ያማከለ፣ ለምንም ዓይነት ሕገወጥ ድርጊት ሰላባ እንዳይሆኑ የማድረግ ሓላፊነት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ እንዳለበት ከአደራ ጭምር ጋር አሳስባለሁ” የሚል ጽሑፍ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።