ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በህወሓት ውስጥ ያለው ሕገ-ወጥ እና ዘራፊ ቡድን በኃይል ተገድደው ወደ ጦርነት የገቡ የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በሰላማዊ መንገድ እየገቡ ናቸው ተባለ።
በአማራ ክልል የሚገኘው ወደ ዳንሻ የገቡት የልዩ ኃይል አባላቱ፣ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ጋር መዋጋታቸው ትክክል እንዳልነበረ እንደሚያምኑም ተናግረዋል።
እኛ የቆምንለት ዓላማ ለትግራይ ሕዝብ ሰላም እና ደህንነት እንጂ ለትሕነግ ሕገ-ወጥ ቡድን አይደለም ያሉት የልዩ ኃይል አባላቱ፣ ወደ አማራ ክልል ከገቡ በኋላም በእንክብካቤ እንደተያዙ ጠቁመው፤ “የትግራይ ሕዝብ በሕገ-ወጡ የትሕነግ ቡድን ከሚደርስበት በደል ለመውጣት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር ሊሰለፍ ይገባዋል” ብለዋል።