ለአዳዲስ ነዳጅ አከፋፋዮች ነዳጅ በዱቤ መስጠት ማቆሙን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ

ለአዳዲስ ነዳጅ አከፋፋዮች ነዳጅ በዱቤ መስጠት ማቆሙን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቀደም ባሉት አመታት ከነዳጅ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ተግባራዊ የነበረው ዱቤ የመስጠት አሠራር አዳዲስ ለሆኑ የነዳጅ አከፋፋዮች  እንዳይፈፀም መደረጉ ተሰማ።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለኩምቢ ኦይል ትሬዲንግ፣ ለድሬ ፔትሮሊክ እና አፍሪካ ለተባሉ ሦስት የነዳጅ አከፋፋዮች ነዳጅ በዱቤ መስጠት ማቆሙን ይፋ አድርጓል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታደሰ ኃይለማርያም ፤ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ነዳጅ በቀጥታ የገንዘብ ክፍያ ለመሸጥ የሚያፈልገውን ቅድመ ሁኔታ ሁሉ አሟልቶ ወደ የእጅ በእጅ ሽያጭ አሠራር በመግባት ላይ በመሆኑ አዳዲስ ለሆኑ የነዳጅ አከፋፋዮች በዱቤ ነዳጅ መስጠት አቁሟል ብለዋል።
ይሁን እንጂ ነዳጅ ሙሉ በሙሉ መስጠት ከቆመ የሀገር እንቅስቃሴ ስለሚቆም፣ ለነባር ነዳጅ አከፋፋዮች እስካሁን ነዳጅ በዱቤ እየተሰጠ ነው ያሉት ሓላፊው፤ አሠራሩ ከሚቀጥለው ዓመት 2014 ዓ.ም መጋቢት 1 ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆንም አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY