ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በከተማዋ አዲስ የነዋሪዎች የመታወቂያ ምዝገባ እና አሰጣጥ እንዲሁም የመሸኛ አገልግሎት ከዛሬ ጥቅምት 30 ቀን ጀምሮ መሰጠት መቆሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ።
የኤጀንሲው የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ዳይክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ፤ አዲስ የነዋሪነት መታወቂያና የመሸኛ መስጠቱ ላልተወሰነ ጊዜ ቢቋረጥም እድሳትና ምትክ መስጠት ግን አለመቋረጡን ገልፀዋል።
ከተማ አስተዳደሩ የነዋሪነት መታወቂያ መስጠቱን ያቆመው ከወቅታዊው ሀገራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ አዳዲስ መታወቂያዎች ተሰጥተው፤ ለተለያዩ እኩይ ዓላማ መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ቁጥጥር ለማድረግ መሆኑንም ተነግሯል።