ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በተለያዮ ሀገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ማስመዝገቡን ተከለትሎ በዓለም ላይ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን ማለፉ ተሰማ።
ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል ያለው ጆንስ ሆፕኪንስ ዮንቨርስቲ፤
ሀገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ የሟቾች ቁጥር ይህን አኃዝ ይበልጣል ሲል ግምቱን አስቀምጧል።
አስቀድሞ የቫይረሱ ሥርጭት ማዕከል የነበረችው አውሮፓ 12.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት፤ 305 ሺኅ 700 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፎፋባት በድጋሚ የቫይረሱ ስርጭቱ ማዕከል ለመሆን ተገዳለች።
በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠችው አሜሪካ 10 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፤ ለተከታታይ ሦስት ቀናትም በቀን ከ125 ሺኅ በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በአሜሪካ የቫይረሱ ስርጭት ጥር መጨረሻ ድረስ መቀነስ ይጀምራል ያሉት አሜሪካዊው ዶክተር ጎትሊብ፤ “ብቸኛው ጥያቄ በዚህ ጊዜ ውስጥ ስንት ሰዎች ይሞታሉ? እና ምን ያህል ሰዎች ይያዛሉ? የሚለው ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
በሌላ በኩል አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ እሁድ እለት 38 ሺኅ 619 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ያስመዘገበች ሲሆን፣ ቅዳሜ ከፍተኛ ሆኖ ከተመዘገበው የ86 ሺኅ 852 ቁጥር ግን በጣም ያነሰ ነው ቢባልም፤ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ መረጃ የመሰብሰብ ችግሮች እንደነበሩበት በመግለጽ ዛሬ እርማት እንደሚደረግበት ጠቁመዋል።