የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ለሁለት መሰንጠቁ፣ ዋና ጸሐፊውም ሓላፊነት መልቀቃቸው ተሰማ

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ለሁለት መሰንጠቁ፣ ዋና ጸሐፊውም ሓላፊነት መልቀቃቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በለውጡ ማግስት ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ወደ ሀገር ቤት በገባው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) አመራሮች ዘንድ አለመግባት መከሰቱን ተከትሎ ግንባሩ ለሁለት እንደተሰነጠቀ በመነገር ላይ ነው።

የግንባሩ አመራሮች መሀል ከአንድ አመት በፊት የተፈጠረው አለመግባባትና የሀሳብ ልዮነት ሥር እየሰደጀ ሄዶ የግንባሩ ዋና ጸሐፊ ከሓላፊነታቸው እስከመልቀቅ ያደረሰ ክስተት ታይቷል።
ግንባሩ ሀገር ውስጥ ከገባ ወዲህ በድርጅቱ  ውስጥ እያጋጠሙ ባሉ የአመራር ችግሮች እና ሥር የሰደደ  መከፋፈልና ቡድንተኝነት የተነሳ ከግንባሩ ዋና ጸሐፊነት በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን የኦብነግ ዋና ጸሐፊ ይፋ ማድረጋቸው ደግሞ ግንባሩ ፍርክስክሱ እየወጣ መሆኑን አመላካች ነው ተብሎለታል።
በድርጅቱሥርዓት፣ ዲሲፒሊንና መርሆዎችን አለመከተል፤ የመልካም አስተዳደር እጦት እንዲሁም ላንዣበቡት ችግሮች መፍትኄ ለማግኘት ይስተዋላል ያሉት ሀሰን ሞላህ (ዋና ጸሐፊ የነበሩ) ፤ የድርጅቱን አንድነት አስጠብቆ በመተማመን እና በቅንነት ሀገርና ህዝብን ለማገልገል ብዙ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውቀዋል።
 ይሁን እንጂ ያደረኩት ጥረት ሁሉ ከንቱ ሆኖ በመቅረቱ በገዛ ፍቃዴ ከሓላፊነት ሥፍራዬ ለቅቄያለሁ በማለት ኦብነግ አደጋ ውስጥ መሆኑን የጠቆሙት የግንባሩ ከፍተኛ አመራር፤ “የድርጅቱን  ነባራዊ ሁኔታ በጥልቅ ከገመገምኩኝ፣  የሚመራበትን  አቅጣጫ በጥሞና ካስተዋልኩኝ በኋላ ፓርቲው በዚህ ዓይነት መንገድ  መፍትኄ መገኘት  እንደማይቻል በግልጽ  ተረድቻለሁ” ብለዋል።

LEAVE A REPLY