ጀነራል እንደሻው ጣሰው የደሕንነት መ/ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ተሰጣቸው

ጀነራል እንደሻው ጣሰው የደሕንነት መ/ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ተሰጣቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ትናንት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው ሹም ሽር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ቀደም ባለው ጊዜ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ሢሠሩ የነበሩት ጀነራል እንዳሻው ጣሰው በቦታቸው ላይ የመረጃና ደሕንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኮማንደር ደመላሽ መመደባቸውን ተከትሎ አዲስ ሹመት ዛሬ ተሰጥቷቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት የአመራር ምደባ መሠረት ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተነሱት ጀነራል እንደሻው ጣሰው ወደ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲዛወሩ ተደርጓል።
ጀነራሉ በከፍተኛ የሓላፊነት ሹመት ተመደበው ወደ ደሕንነት መ/ቤቱ እንዲዛወሩ መደረጋቸው ይገለፅ እንጂ እስካሁን የሥልጣን እርከናቸው ይፋ አልተደረገም። ይሁን እንጂ ለጉዳዮ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጀነራል እንደሻው ጣሰው የአቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ሆነው መመደባቸውን ይናገራሉ።

LEAVE A REPLY