ሽራሮ ላይ እጅና እግራቸው ታስሮ የተረሸኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት አስከሬን ተገኘ

ሽራሮ ላይ እጅና እግራቸው ታስሮ የተረሸኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት አስከሬን ተገኘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የምዕራቡ የትግራይ ክልል ቀጠና ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ነፃ መውጣቱንጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አረገዘች ገጡ።

የመከላከያ ሠራዊቱ ሽራሮን በተቆጣጠረበት ወቅት እጅና እግራቸውን የፈጢኝ ታስረው የተረሸኑ የመከላከያ አባላትን አግኝተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስግብግቡ ጁንታ የፈጸመው ግፍና ጭካኔ ልብ ሰባሪ እንደሆነም አስረድተዋል።
ሠራዊቱ በየቦታው ሲደርስ ከዚህ የከፋ ጭካኔና ግፍ ሊያጋጥመን ይችላል ያሉት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለጁንታው ግን የመጨረሻው ነው ሲሉም ተደምጠዋል።
“ሙት ይዞን እንዳይሞት ግፍና ጭካኔውን ለዓለም ፈጥነን ማጋለጥ አለብን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ግፍና በደላቸው ሕዝብና ሠራዊቱን አስቆጥቶ ለበቀል እርምጃ ለማነሳሳት የታለመ ቢሆንም፤ ሕዝቡና ሠራዊቱ   ሁኔታውን በሠፊ ልቦና ማስተናገዳቸውን ዛሬ በቲውተር ገጻቸው ላይ አስነብበዋል።
የጁንታው ዋና ዓላማ  ኢትዮጵያን መስበር ነው ያሉት የብልፅግናው መሪ ይህ ግን መቼም ሊሆን እንደማይችል ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY