በአማራ ክልል ከተሞች ለነገ የተጠራው ሰልፍ መሰረዙ ተነገረ

በአማራ ክልል ከተሞች ለነገ የተጠራው ሰልፍ መሰረዙ ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኅዳር 3 ቀን በተለያዮ የአማራ ክልል ከተሞች እንዲካሄድ የተጠራው ሰልፍ ተሰረዘ።

የክልሉ መንግሥት ከደቂቃዎች በፊት በሰጠው አዲስ መግለጫ መሰረት በተመረጡ የክልሉ  የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለሌላ ላልታወቀ ጊዜ ተራዝሟል ሲል መሰረዙን ይፋ አድርጓል።
ሰልፉ የፌደራሉ መንግሥት በሕወሓት ታጣቂ ቡድን ላይ እየወሰደ የሚገኘውን ሕግ የማስከበር እርምጃ ለመደገፍ በሚል የተዘጋጀ የነበረ ቢሆንም፣ በችኮላ የድጋፍ ሰልፍ ለማካሄድ የተሯሯጡት የብልፅግና አመራሮች ዛሬ ማምሻውን ለሁለተኛ ጊዜ በሰጡት መግለጫ ሰልፉ እንደተሰረዘ ተናግረዋል።
በርካታ ኢትዮጵያውያን ከወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ አንጻር ሰልፉ ዜጎችን ለጥፋት ኃይሎች ጥቃት እንዲመቹ ሊያደርግ ይችላል በሚል ሲቃወሙት መዋላቸው አይዘነጋም። በርግጥም በአማራና ኦሮሚያ ክልል፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል የተባለው ሰልፍን ጁንታውና የጥፋት አጋሩ ኦነግ ሸኔ ሰላማዊ ዜጎችን ለማጥቃት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ይገመታል።

LEAVE A REPLY