የህወሓት ተላላኪዎች ናቸው የተባሉ 242 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነገረ

የህወሓት ተላላኪዎች ናቸው የተባሉ 242 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ 150 በሕወሓት ተላላኪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተሰማ።

ግጭቶችን በማነሳሳትና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶችን የማካሄድ ተልዕኮ ነበራቸው  የተባሉ ተጠርጣሪዎች ናቸው የተያዙት።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ እንዳለው ከሆነ የህወሓት የላካቸው ወንጀለኞች በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ ባቋቋመው መረብ መሆኑ ታውቋል።
የታሰሩት ግለሰቦች የተለያዩ ብሔር ተወላጆች መሆናቸውን የጠቆመው መግለጫ፤ ከተጠርጣሪዎች መካከል ጥቂቶቹ የፀጥታ ስጋትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዋስ መለቀቃቸው ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY