38 የህወሓት አባላት ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ፓርላማው ዛሬ በሙሉ ድምፅ ወሰነ

38 የህወሓት አባላት ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ፓርላማው ዛሬ በሙሉ ድምፅ ወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አራተኛ መደበኛ ስብሰባ የ38 ግለሰቦችን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን የእነዚህን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ነው ምክር ቤቱ የውሳኔ ሐሳቡን በሙሉ ድምፅ ያፀደቀው።
በመሆኑም የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤልን  ጨምሮ የ38 ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት ተነስቷል።
ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ከተደረገባቸው ግለሰቦች መካከል ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ይገኙበታል። ከእነዚህም መካከል አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ፣ አቶ አባይ ፀሐዬ፣ ዶክተር አምባሳደር አዲስዓለም ቤሌማ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አቶ አፅበሃ አረጋዊ፣ አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ እና ሌሎችም እንደተካተቱበት ታውቋል።
የጁንታው ቡድን አባልና ተልዕኮ አስፈጻሚ የሆኑት ግለሰቦችን ዐቃቤ ሕግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የጠየቀው ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት የተጠረጠሩ በመሆናቸው ነው።
የፌደራል መንግሥት የትግራይ ክልልን በሚመራው ህወሓት አማካይነት በሰሜን እዝ ሥር በሚገኘው የሀገሪቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ጠቅሶ ሕግን ማስከበር ያለውን ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን መግለጹ አይዘነጋም።

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ስም ዝርዝርም:-

1. ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
2. አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ
3. አቶ አባይ ጸሀዬ
4. አምባሳደር ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ
5. አቶ ጌታቸው ረዳ
6. አቶ አጽብሃ አረጋዊ
7. አቶ ታደሰ ሀይሌ
8. ዶ/ር መብራቱ መለስ
9. ወ/ሮ ለምለም ሀድጉ
10. አቶ ገ/እግዚአብሄር አርኣያ
11. አቶ ሀለፎም ግደይ
12. አቶ ሀዱሽ አዛነው
13. ወ/ሮ መብራት ገ/ጊዮርጊስ
14. ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሄር
15. ወ/ሪት ልዕልቲ ጸጋዬ
16. ወ/ሮ ማሚት ተስፋይ
17. ወ/ሮ ማና አብርሃ
18. አቶ ካላዩ ገ/ህይወት
19. አቶ ጌዲዮን ሀ/ስላሴ
20. መ/ር በርሄ ዝግታ
21. አቶ ታደለ አሰፋ
22. አቶ ነጋ አሰፋ
23. ወ/ሮ ናፈቁሽ ደሴ
24. ወ/ሮ ሽሻይ ሀ/ሰላሴ
25. ወ/ሮ አልማዝ አርኣያ
26. ወ/ሮ አሰለፈች በቀለ
27. ወ/ሮ አስቴር አማረ
28. አቶ አለምሰገድ ወረታ
29. ዶ/ር አድሃና ሃይለ
30. አቶ ኪሮስ ወ/ሚካኤል
31. አቶ ሹምዬ ገብሬ
32. አቶ ካሳ ጉግሳ
33. ወ/ሮ አበራሽ አድማሱ
34. አቶ ዮሀንስ በቀለ
35. አቶ ዳኘው በለጠ
36. ወ/ሮ ፅዋሃብ ታደሰ
37. አቶ ዊንታ ተክሉ እና
38. አቶ ግርማይ ሻዲ
መሆናቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY