የትግራይ ልዮ ኃይል አባላት በሦስት ቀን ውስጥ እጅ እንዲሰጡ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ...

የትግራይ ልዮ ኃይል አባላት በሦስት ቀን ውስጥ እጅ እንዲሰጡ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቀጣዮቹ ሦስት ቀናት ውስጥ እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊቱ እንዲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ባስተላለፉት መልእክት የጁንታው አባላት ጦር ግንባር ወጥተው መምራት ከማይችሉበት አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡና እንደተከበቡም አስረድተዋል።
“የተከበርክ የትግራይ ህዝብ ሆይ እነዚህ ሽፍቶች እንኳን ጦርነት ውስጥ ገብተው ሊዋጉ ይቅርና የጥይት ድምፅ እንኳን መስማት አይፈልጉም” ሲሉ በትግርኛ ቋንቋ ለሠፊው የትግራይ ሕዝብ መልእክት ያስተላለፉት  ዶክተር ዐቢይ፤ በተሳሳተ የፖለቲካ መንገድ እሳት ውስጥ እንዲማገድ እየተደረገ ያለው የክልሉ ልዮ ኃይል በሦስት ቀን ውስጥ እጁን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY