ዶ/ር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሾሙ

ዶ/ር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሾሙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  ዶክተር ሙሉ ነጋን የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርገው መሾማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔና በሚኒስትሮች ምክር የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደርን በተመለከተ በወጣው ደንብ መሠረት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶ/ር ሙሉ፤ በክልሉ በህጋዊነት ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የክልሉን መንግሥት ሥራ አስፈጻሚ መዋቅሮች የሚመሩ ሓላፊዎችን መልምለው ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 ከሚያዚያ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዮት አዲሱ የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በተለያዮ የሥራ ሓላፊነቶች ላይ አገልግለዋል።

LEAVE A REPLY