ኢትዮጵያ ነገ ዜና || “ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል ለመከላከያ ሠራዊት ክብር የመግለጽ መርሓ-ግብር እንደሚካሄድ ተነገረ።
የፊታችን ማክሰኞ ኅዳር 8/2013 ዓ.ም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለአንድ ደቂቃ በየቤቱ እና በየመሥሪያ ቤቱ በር ላይ ቀኝ እጁን በደረቱ ላይ በማድረግና በግራ እጅ ባንዲራ በመያዝ፣ ቆሞ ለመከላከያ ሠራዊት ክብር የሚገልፅበት ፕሮግራም ተይዟል።
ሀገራዊ ክብር የመግለጽ መርሓ-ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በአንድነት ፓርክ ከቀኑ 5:30 ላይ እንደሚጀመርም ከተያዘው ቅድመ መርኃ ግብር መረዳት ተችሏል።
ለተከታታይ ቀናት በሚካሄደው ሀገራዊ ዘመቻ ላይ በሌሎች ቀናት ለአንድ ደቂቃ በክብር እጅ የመንሳት ቀን፣ የማጨብጨብ፣ የመዝሙር፣የሙዚቃ ኮንሰርት የገቢ ማሰባሰቢያና መአድ ማጋራትን የመሳሰሉ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ።