በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ምክንያት ርችት መተኮስ ተከለከለ

በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ምክንያት ርችት መተኮስ ተከለከለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በልዩ ልዩ ምክንያት ርችት መተኮስ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

አንዳንድ ግለሰቦችና ተቋማት ልዩ ልዩ ፕሮግሞችን ምክንያት በማድረግ  ርችት እየተኮሱ በመሆኑ፤ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ካለችበት የፀጥታ ሁኔታ በምንም አይነት ምክንያት ርችት መተኮስ የተከለከለ ነው ያለው ኮሚሸኑ፤ አ ይህንን መልእክት በመተላለፍ  ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ በህግ ይጠየቃል ብሏል።
ለህግ መከበር ነዋሪው እያደረገ ላለው ቀና ትብብር  ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅም አሳስቧል።

LEAVE A REPLY