የማይካድራውን ጭፍጨፋ የሚያጣራ ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩን ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ገለፀ

የማይካድራውን ጭፍጨፋ የሚያጣራ ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩን ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽኝ በማይካድራ የተፈጸመውን ሰብአዊ ቀውስ በአፋጣኝ ለማጣራት የምርመራ ቡድን ወደ ሥፍራው ላከ።

ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው ጦርነት እና የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫው በግጭቱ በተሳተፉ ማንኛውም ወገኖች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በመመርመር እና ማስረጃ በማሰባሰብ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እሠራለሁ ብሏል።
የትግራይ ክልልን በተመለከተ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይል በአፋጣኝ፣ የሰብኣዊ እርዳታ ጉዳይ ዴስክ እንዲያቋቁም እና ከሰብኣዊ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ጋር ምክክር እንዲጀመርም ኮሚሽኑ ከወዲሁ አሳስቧል።
የቀይ መስቀል ማኅበር ሰብኣዊ አገልግሎቶችን ማከናወን እንዲችል በውጊያው ተሳታፊ የሆኑ አካላት ተፈፃሚነት ባላቸው ዓለም ዐቀፍ ሕጎች መሰረት የቀይ መስቀል አርማ እንዲያከብሩና ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉም የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን በስተመጨረሻ አሳስቧል።

LEAVE A REPLY