ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዮ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት የነበራቸው 14 የአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉተ
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደገለፀው ከሆነ፤ አልሸባብ እና አይ ኤስ አባሎቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እና የተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመላክ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት በመፈፀም በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳይ ለማድረስ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ተቋሙ ባደረገው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል 14 የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎችን መያዝ ተችሏል።
የጥፋት ተግባሩን ለመፈፀም ሀገር ውስጥ የገባው የአልሸባብ የሽብር ቡድን አብዱል አብዲ ጀማል በቅፅል ስሙ አብዱልቃድር የተባለ ተጠርጣሪ አንዱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የአልሸባብን የሽብር ህዋስ ሲያስተባብር የነበረና፤ በሶማሊያ ከሚገኘው ጃፋር ወይም ጉሬ ከተባለ የአልሸባብ ከፍተኛ አመራር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በመፍጠርና ስምሪት በመቀበል በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ሲንቀሳቀስ መሰንበቱም ታውቋል።