ዋጃና ጥሙጋ አካባቢዎች ከጁንታው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ነፃ ወጡ

ዋጃና ጥሙጋ አካባቢዎች ከጁንታው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ነፃ ወጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጥቃቱን አጠናክሮ የቀጠለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና እና የአማራ ልዩ ኃይል ከአላማጣ በቅርብ ርቀት የሚገኙትን  የዋጃ እና ጥሙጋን  አካባቢዎች መቆጣጠሩ ተሰማ።

ከጁንታው ነጻ ከወጡት ቦታዎች ባሻገር ቁጥራቸው በርከት የቡድኑ አባላት እጃቸውን መስጠታቸው ተነግሯል።

የሕወሓት ቡድን ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ጭቆናና በደል ሲያደርስባቸው መቆየቱን የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች

ዛሬ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይልና በሚሊሻ አባላት ጋር በመሆን ደስታቸውን ሲገልጹ በአማራ መገናኛ ብዙኃን ላይ በስፋት ታይተዋል።

LEAVE A REPLY