በአሜሪካና አውሮፓ ያሉ ሠባት የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ለዓለም ዐቀፍ ተቋማት ደብዳቤ ጻፉ

በአሜሪካና አውሮፓ ያሉ ሠባት የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ለዓለም ዐቀፍ ተቋማት ደብዳቤ ጻፉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  በሰሜን አሜሪካና  በአውሮፓ የሚገኙ ሠባት የኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት የህግ የበላይነትን ለማስከበር፣ የአሸባሪውንና የከሃዲውን  የህወሓት መሪዎች ወደ ህግ ፊት ለማቅረብ በትግራይ ውስጥ የጀመረውን ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ በማስመልከት ነው ለዓለም ዐቀፍ ማኅበረሰብ መልእክት ያስተላለፉት።

እነዚህ ሲቪክ ማኅበራት በጋራ ያወጡትና አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለውን እውነት ያሳዮበት ባለ ሦስት ገጽ ደብዳቤን ለተባበሩት መንግሥታት፣ ለአፍሪካ ኅብረት፣ ለዓለም ዐቀፍ ሚዲያ ተቋማት፣ ለልዩ ልዩ ዓለም  ዐቀፍ ተቋማት አድርሰዋል።
መቀመጫቸውን በውጭው ዓለም ያደረጉት እነዚህ ሠባት ሲቪክ ማኅበራት በጋራ ያወጡት መግለጫና የጻፉት ደብዳቤ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ሀቁን እንዲረዳ በማድረግ ረገድ አስተዋፅዖው የጎላ ነው ተብሎለታል።

LEAVE A REPLY