ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ ክልል የሚካሄደው የህግ የበላይነትን የማስከበር ሥራን በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ያለ ማንም እገዛና ድጋፍ ኢትዮጵያ ብቻዋን ጁንታውን ማንበርከክ እንደምትችል አረጋገጡ።
“ፍትሕ ታሸንፋለች፤ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች የሐሰተኛው አጥፊ ቡድን መጨረሻ ተቃርቧል ” ሲሉ የህወሓት አመራሮች ቀጣይ እጣ ፈንታን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሕግ የበላይነትን በማስከበር፣ ተያይዞም ሀገራችንን በመዝረፍ እና ሰላሟን በማወክ የተሰማሩትን ተጠያቂ በማድረግ፣ ለዘላቂ ሰላም እና ሕብረት የሚሆን ጠንካራ መሠረት እንገነባለን ብለዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት የታዩት ሁኔታዎች በህወሓት ውስጥ ያለውን አጥፊ ቡድን ትክክለኛ ማንነት የገለጡ መሆናቸውን የተናገሩት የብልፅግና መሪ፤ መከላከያ ሠራዊቱ የመጨረሻውን ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።