ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የነባር እና አዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በአዲሱ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት እድሳት እና ምዝገባ ለማከናወን ፓርቲዎች ያቀረቡትን የአባላት ፊርማ እና ሰነድ እየመረመረመርኩ ነው አለ።
ቦርዱ በአዲሱ የምርጫ ምዝገባ አዋጅ መሰረት ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው የተገኙ 76 ነባር የፖለቲካ ፓርቲዎችን የፖለቲካ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ሰነድ ምርመራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ቦርዱ ከተለያዮ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታና ጥያቄዎችን በተመለከተም በቅርቡ ምላሽ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።