ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በታጣቂዎችቅዳሜ ዕለት በመተከል ዞን በደባጤ ወረዳ ከወንበራ ወደ ቻግኒ በመጓዝ ላይ በነበረ አውቶብስ ላይ ታጣቂዎች ዘግናኝ ጥቃት ተፈጽሞ ቢያንስ 34 ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን አረጋገጠ።
የጥቃት ሰለባዎቹ ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል የተናገሩት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ “ይህ ጥቃት ሁላችንም በጋራ የተሸከምነውን የሰው ሕይወት ክፍያ ዛሬም በአሳዛኝ ሁኔታ የሚያሻቅብ ነው። የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በፍጥነት ጥቃቱ የበለጠ እንዳይባባስ እርምጃ መውሰዳቸው አበረታች ነው” ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ቀደም ሲል በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ያምፕ ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች በነዋሪዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ አንድ ነዋሪ ሲገደል፣ ሁለት የክልሉ የፖሊስ አባላት እንዲሁም የወረዳው አስተዳዳሪ መቁሰላቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሸን ሓላፊ መናገራቸው ይታወቃል።